የስደተኞች ምላሽ ሰጭ ፖሮግራም የሚመረቅበት ዝግጅት በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

ጅግጅጋ (cakaaranwes)ሀሙስ ግንቦት 2 ቀን 2010ዓ.ም.የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ምላሽ ከፍተኛ ኮሚሽን/UNHCR የዘንድሮ ሪፖርት እንደሚያሳየው በአፍሪካ ስደተኞች ከሚያስተናገዱ ሃገራት አንጻር ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀዳሚነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ስደተኞች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአግባቡ የሚታስተናግድ ሲሆን በሀገሪቱ 26 የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያዎችይገኛሉ።

በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በርካታ ቁጥር ያለቸው የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያዎች ስለሚገኙ የስደተኞች ምላሽ ሰጭ ፖሮግራም  የሚመረቅበት ልዩ ዝግጅት በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደዋል።በሥነ-ስርዓቱ ላይም የኢሶክመ.የውሃ ልማት ቢሮ ሃላፊ፤የኢፌዴሪ የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አስተዳደር አጄንሲ/ARRA ም/ዳይረክተር፤የዓለም ባንክ ተወካዮች፤የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ምላሽ ከፍተኛ ኮሚሽን/UNHCR ከፍተኛ አመራር አካላት፤የሀገር ውስጥ ግብረሰናይ ድርጅቶች አመራር ባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ የልሆኑ እንግዶችም ተገኝተዋል።

በዚህም የኢፌዴሪ የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ጉዳዮች አስተዳደር አጄንሲ/ARRA ም/ዳይረክተር አቶ ዛይኑ ጀማል በክልሉ የተጀመረው የስደተኞች ምላሽ ሰጭ ፖሮግራም ለክልሉ ህዝብና በክልሉ የሚገኙ ስደተኞችም ከፍተኛ ጥቅምና ፋይዳ ያለው ከመሆኑ ባሻገር ኢትዮጵያ ስደተኞች ለማስስተናገድ የክልሉ መንግስት ለድርጅታቸው ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገላቸው ገልጿል።

 በተጨማሪም የኢሶክመ.የውሃ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ አብዲ በክልሉ በርካታ የስደተኞች መጠሊያ ጣቢያዎች እንደ ዶሎአዶ፤በቆልማዮ፤ቀብሪበየህ፤ሼድዴርና የመሳሰሉት አከባቢዎች እንደሚገኙና ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም እንደሚኖሩና የስደተኞች ምላሽ ሰጭ ፖሮግራም ከስደተኞች በዘለል ለክልሉ ህዝብም ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።