12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ምክክር መድረክ በአውበሬ ከተማ በይፋ ተጀመረ

አውበሬ (Cakaaranews) ቅዳሜ፤ግንቦት 04/2010..12ኛውየኢትዮጵያሶማሌ  ክልል ህዝብና መንግስት የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳድርና የህዳሴ ትራንስፎርሜሽን ጉባኤ በፋፈን ዞን በአውበሬ ወረዳ መዲና በሆነችው በአውበሬከተማ በይፋ ተጀመረ።በምክክሩ ላይም  ከክልሉ 11 ዞኖች፣ከ6ቱ የከተማ መስተዳደሮችና ከ93 ወረዳዎች የመጡ የማህበሰብ ክፍሎች እንደ ወጣቶች፤አገር ሽማግሌዎች፤እምነት አባቶች፤ሴቶችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡና  ከ4000 በላይ የሚሆኑ ታዳሚዎች በማሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ 

 በተጨማሪም በ12ኛውየኢትዮጵያሶማሌመንግስትናህዝብምክክር መድረክ ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ.እና የኢሶህዴፓ ከፍተኛ አመራር አካለት የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ ኡመር፣ የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤና የኢሶህዴፓ ድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ፣ የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ  ክብርት ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋረህ፣ የክልሉ  ም/ፕሬዝዳንትና የጤና ቢሮ  ኃላፊ  አቶ ሀምዲ አደን ሀምዲ፣ የክልሉ መንግስት ቢሮ ሀላፊዎች፣ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች እና ከመላው የክልሉ ዞኖች፣የከተማ መስተዳደሮችና ከክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ3000 በላይ የሚሆኑ የማህበሰብ ክፍሎች እንደ ሀገር ሸማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ዲያስፖራ አባላት፣ የክልሉ ባህል ባንድ ቡድኖች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተካፍለዋል፡፡

 በሌላ በኩል በጉባኤው መክፈቻ ላይ የ2010ዓ.ም የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና ክልሉ መንግስት  ቀደም ብሎ ክልሉ ያሳለፈበት የሰላምና ልማት እጦት አስመልክቶ ወሳኝ ታሪካዊ  ሪፖርት ያቀረቡት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር  በክልሉ የነበረው የሰላም፤የልማትና የመልካም አሰተዳደር እንግልቶች በሰፊው ትንታኔ ሰጥቶበታል።አያይዞም የቀድሞ ብልሹ አመራር አካላት ያስከተሉት በርካታ የሰላም፤የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በክልሉ ጠንካራና አስታዋይ ህዝብ ያለፍነበት መሆኑን በመግለፅና በቀጣይ ቀናት በመድረኩ በአጠቃላይ በክልሉ መንግስት የተከናወኑት የሰላም፤የልማት፤የመልካም አስተዳደር፤የክልሉ ህዳሴ ትራንስፎርሜሽን እንደሁም በክልሉ ከተሞች የሚታዩ የመስረተ ልማት እንቅፋቶች ከህዝቡ ጋር እንደሚወያይበት ክቡር ፕሬዝዳንቱ ገልጿል ።

 

በመጨረሻም መድረኩ በክልሉና በአውበሬ ከተማ ባህል ባንዶች በክልሉ መሪ ፓርቲ በኢሶህዴፓና በክልሉ መንግስት በጥቅት አመታት ውስጥ በክልሉ ሰላም፤ልማት፤መልካም አስተዳደር እንዲሁም በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በሀገሪቱ ህዳሴ ትራንስፎርማሽን ተግባራት ዙሪያ ያዘጋጁት ደማቅ ሙዝቃዎች ታጅቦ እንደነበረም የክልሉ ሚዲያ አውተራት ገልጿል።